ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #13
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 13

Exodus 13

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማሕፀንን የሚከፈት በኵር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ የእኔ ነው።

2 Sanctify unto me all the firstborn, whatsoever openeth the womb among the children of Israel, both of man and of beast: it is mine.

3 ሙሴም ሕዝቡን አለ። ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስቡ፥ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።

3 And Moses said unto the people, Remember this day, in which ye came out from Egypt, out of the house of bondage; for by strength of hand the Lord brought you out from this place: there shall no leavened bread be eaten.

4 እናንተ ዛሬ በአቢብ ወር ወጥታችኋል።

4 This day came ye out in the month Abib.

5 እግዚአብሔርም ለአንተ ይሰጣት ዘንድ ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ምድር ባገባህ ጊዜ ይህችን አምልኮ በዚህ ወር ታደርጋለህ።

5 And it shall be when the Lord shall bring thee into the land of the Canaanites, and the Hittites, and the Amorites, and the Hivites, and the Jebusites, which he sware unto thy fathers to give thee, a land flowing with milk and honey, that thou shalt keep this service in this month.

6 ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላለህ፥ በሰባተኛውም ቀን ለእግዚአብሔር በዓል ይሆናል።

6 Seven days thou shalt eat unleavened bread, and in the seventh day shall be a feast to the Lord.

7 ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ እንጀራ ትበላለህ፥ በአንተም ዘንድ እርሾ ያለበት እንጀራ አይታይ፥ በድንበርህም ሁሉ እርሾ አይታይ።

7 Unleavened bread shall be eaten seven days; and there shall no leavened bread be seen with thee, neither shall there be leaven seen with thee in all thy quarters.

8 በዚያም ቀን፦ ከግብፅ በወጣሁ ጊዜ እግዚአብሔር ስላደረገልኝ ነው ስትል ለልጅህ ትነግረዋለህ።

8 And thou shalt shew thy son in that day, saying, This is done because of that which the Lord did unto me when I came forth out of Egypt.

9 እግዚአብሔር በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶሃልና የእግዚአብሔር ሕግ በአፍህ ይሆን ዘንድ በእጅህ እንደ ምልክት በዓይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ።

9 And it shall be for a sign unto thee upon thine hand, and for a memorial between thine eyes, that the Lord’s law may be in thy mouth: for with a strong hand hath the Lord brought thee out of Egypt.

10 በዓመት በዓመት በወራቱ ይህችን ሥርዓት ጠብቃት።

10 Thou shalt therefore keep this ordinance in his season from year to year.

11 እግዚአብሔርም ለአንተ ለአባቶችህም እንደ ማለ ወደ ከነዓናውያን ምድር ባገባህ ጊዜ፥ እርስዋንም በሰጠህ ጊዜ፥

11 And it shall be when the Lord shall bring thee into the land of the Canaanites, as he sware unto thee and to thy fathers, and shall give it thee,

12 ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ለይ ከሚሆንልህ ከብት ሁሉ ተባት ሆኖ አስቀድሞ የተወለደው ለእግዚአብሔር ይሆናል።

12 That thou shalt set apart unto the Lord all that openeth the matrix, and every firstling that cometh of a beast which thou hast; the males shall be the Lord’s.

13 የአህያውን በኵር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ባትዋጀውም አንገቱን ትሰብረዋለህ የሰውንም በኵር ሁሉ ከልጆችህ መካከል ትዋጀዋለህ።

13 And every firstling of an ass thou shalt redeem with a lamb; and if thou wilt not redeem it, then thou shalt break his neck: and all the firstborn of man among thy children shalt thou redeem.

14 እንዲህም ይሆናል በሚመጣው ጊዜ ልጅህ። ይህ ምንድር ነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ። እግዚአብሔር በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር አወጣን

14 And it shall be when thy son asketh thee in time to come, saying, What is this? that thou shalt say unto him, By strength of hand the Lord brought us out from Egypt, from the house of bondage:

15 ፈርዖንም እንዳይሰድደን ልቡን ባጸና ጊዜ እግዚአብሔር ከሰው በኵር ጀምሮ እስከ እንስሳ በኵር ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ ገደለ ስለዚህ ወንድ ሆኖ ማሕፀንን የከፈተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ፥ ነገር ግን የልጆቼን በኵር ሁሉ እዋጃለሁ።

15 And it came to pass, when Pharaoh would hardly let us go, that the Lord slew all the firstborn in the land of Egypt, both the firstborn of man, and the firstborn of beast: therefore I sacrifice to the Lord all that openeth the matrix, being males; but all the firstborn of my children I redeem.

16 እግዚአብሔርም በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶናልና በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዓይኖችህም መካከል እንደ ተንጠለጠለ ነገር ይሁንልህ።

16 And it shall be for a token upon thine hand, and for frontlets between thine eyes: for by strength of hand the Lord brought us forth out of Egypt.

17 እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም እግዚአብሔር፦ ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብፅም እንዳይመለስ ብሎአልና።

17 And it came to pass, when Pharaoh had let the people go, that God led them not through the way of the land of the Philistines, although that was near; for God said, Lest peradventure the people repent when they see war, and they return to Egypt:

18 ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ምድር ተሰልፈው ወጡ።

18 But God led the people about, through the way of the wilderness of the Red sea: and the children of Israel went up harnessed out of the land of Egypt.

19 ዮሴፍም። እግዚአብሔር ሳይጎበኛችሁ አይቀርም፥ አጥንቶቼንም ከዚህ ከእናንተ ጋር ታወጣላችሁ ብሎ የእስራኤልን ልጆች አምሎአቸው ነበርና ሙሴ የእርሱን አጥንቶች ከእርሱ ጋር ወሰደ።

19 And Moses took the bones of Joseph with him: for he had straitly sworn the children of Israel, saying, God will surely visit you; and ye shall carry up my bones away hence with you.

20 ከሱኮትም ተጓዙ፥ በምድረ በዳውም ዳር በኤታም ሰፈሩ።

20 And they took their journey from Succoth, and encamped in Etham, in the edge of the wilderness.

21 በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ፥ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ።

21 And the Lord went before them by day in a pillar of a cloud, to lead them the way; and by night in a pillar of fire, to give them light; to go by day and night:

22 የደመና ዓምድ በቀን፥ የእሳት ዓምድ በሌሊት ከሕዝቡ ፊት ከቶ ፈቀቅ አላለም።

22 He took not away the pillar of the cloud by day, nor the pillar of fire by night, from before the people.