ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #37
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 37

Exodus 37

1 ባስልኤልም ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ ርዝመቱም ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ።

1 And Bezaleel made the ark of shittim wood: two cubits and a half was the length of it, and a cubit and a half the breadth of it, and a cubit and a half the height of it:

2 በውስጥም በውጭም በጥሩ ወርቅ ለበጠው በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አደረገለት።

2 And he overlaid it with pure gold within and without, and made a crown of gold to it round about.

3 አራት የወርቅ ቀለበቶችም አደረገለት እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኖረ። በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላውም ወገን ሁለት ቀለበቶች ሆኑ።

3 And he cast for it four rings of gold, to be set by the four corners of it; even two rings upon the one side of it, and two rings upon the other side of it.

4 መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠራ፥ በወርቅም ለበጣቸው።

4 And he made staves of shittim wood, and overlaid them with gold.

5 ታቦቱንም ለመሸከም በታቦቱ አጠገብ ባሉት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አገባ።

5 And he put the staves into the rings by the sides of the ark, to bear the ark.

6 ከጥሩ ወርቅም ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ሠራ።

6 And he made the mercy seat of pure gold: two cubits and a half was the length thereof, and one cubit and a half the breadth thereof.

7 ሁለት ኪሩቤልንም ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሠራ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን አደረጋቸው።

7 And he made two cherubims of gold, beaten out of one piece made he them, on the two ends of the mercy seat;

8 ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርጎ በአንድ ላይ ሠራቸው።

8 One cherub on the end on this side, and another cherub on the other end on that side: out of the mercy seat made he the cherubims on the two ends thereof.

9 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ የዘረጉ ሆኑ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ሸፈኑ፥ እርስ በርሳቸውም ተያዩ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ መክደኛው ተመለከቱ።

9 And the cherubims spread out their wings on high, and covered with their wings over the mercy seat, with their faces one to another; even to the mercy seatward were the faces of the cherubims.

10 ርዝመቱ ሁለት ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነውን ገበታ ከግራር እንጨት ሠራ።

10 And he made the table of shittim wood: two cubits was the length thereof, and a cubit the breadth thereof, and a cubit and a half the height thereof:

11 በጥሩም ወርቅ ለበጠው፥ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አደረገለት።

11 And he overlaid it with pure gold, and made thereunto a crown of gold round about.

12 በዙሪያውም አንድ ጋት የሚያህል ክፈፍ አደረገለት የወርቅም አክሊል በክፈፉ ዙሪያ አደረገለት።

12 Also he made thereunto a border of an handbreadth round about; and made a crown of gold for the border thereof round about.

13 አራትም የወርቅ ቀለበቶች አደረገለት ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮቹ ባሉበት በአራቱ ማዕዘኖች አደረገ።

13 And he cast for it four rings of gold, and put the rings upon the four corners that were in the four feet thereof.

14 ገበታውንም ለመሸከም መሎጊያዎቹ እንዲሰኩባቸው ቀለበቶች በክፈፉ አቅራቢያ ነበሩ።

14 Over against the border were the rings, the places for the staves to bear the table.

15 ገበታውንም ይሸከሙባቸው ዘንድ መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።

15 And he made the staves of shittim wood, and overlaid them with gold, to bear the table.

16 ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ በገበታው ላይ የሚኖሩትን ዕቃዎች፥ ወጭቶቹንና ጭልፋዎቹን ጽዋዎቹንም መቅጃዎቹንም፥ ከጥሩ ወርቅ አደረጋቸው።

16 And he made the vessels which were upon the table, his dishes, and his spoons, and his bowls, and his covers to cover withal, of pure gold.

17 መቅረዙንም ከጥሩ ወርቅ አደረገ መቅረዙንም ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ ጽዋዎቹን፥ ጕብጕቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ።

17 And he made the candlestick of pure gold: of beaten work made he the candlestick; his shaft, and his branch, his bowls, his knops, and his flowers, were of the same:

18 በስተ ጎኑም ስድስት ቅርንጫፎች ወጡለት ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስቱም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ወጡ።

18 And six branches going out of the sides thereof; three branches of the candlestick out of the one side thereof, and three branches of the candlestick out of the other side thereof:

19 በአንደኛው ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ።

19 Three bowls made after the fashion of almonds in one branch, a knop and a flower; and three bowls made like almonds in another branch, a knop and a flower: so throughout the six branches going out of the candlestick.

20 በመቅረዙም ጕብጕቦቹንና አበቦቹን አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች አደረገ።

20 And in the candlestick were four bowls made like almonds, his knops, and his flowers:

21 ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ከሁለትም ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ ነበረ።

21 And a knop under two branches of the same, and a knop under two branches of the same, and a knop under two branches of the same, according to the six branches going out of it.

22 ጕብጕቦቹና ቅርንጫፎቹ ከእርሱ ጋር አንድ ነበሩ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተቀረጸ ከጥሩ ወርቅ ተሠርቶ ነበር።

22 Their knops and their branches were of the same: all of it was one beaten work of pure gold.

23 ሰባቱንም መብራቶች መኰስተሪያዎቹንም፥ የኩስታሪ ማድረጊያዎቹንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።

23 And he made his seven lamps, and his snuffers, and his snuffdishes, of pure gold.

24 መቅረዙንም ዕቃውንም ሁሉ ከአንድ መክሊት ጥሩ ወርቅ አደረገ።

24 Of a talent of pure gold made he it, and all the vessels thereof.

25 የዕጣን መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ፥ አራት ማዕዘን ነበረ ከፍታውም ሁለት ክንድ ነበረ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር በአንድነት የተሠሩ ነበሩ።

25 And he made the incense altar of shittim wood: the length of it was a cubit, and the breadth of it a cubit; it was foursquare; and two cubits was the height of it; the horns thereof were of the same.

26 ላይኛውንና የግድግዳውንም ዙሪያ ቀንዶቹንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገበት።

26 And he overlaid it with pure gold, both the top of it, and the sides thereof round about, and the horns of it: also he made unto it a crown of gold round about.

27 ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አደረገበት፥ በዚህና በዚያ በሁለቱም ጎን አደረጋቸው ለመሸከምም የመሎጊያዎች ስፍራ ነበሩ።

27 And he made two rings of gold for it under the crown thereof, by the two corners of it, upon the two sides thereof, to be places for the staves to bear it withal.

28 መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት አደረገ፥ በወርቅም ለበጣቸው።

28 And he made the staves of shittim wood, and overlaid them with gold.

29 የተቀደሰውንም የቅብዓቱን ዘይት፥ ጥሩውንም የጣፋጭ ሽቱ ዕጣን በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ አደረገ።

29 And he made the holy anointing oil, and the pure incense of sweet spices, according to the work of the apothecary.