ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #42
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 42

Genesis 42

1 ያዕቆብም በግብፅ እህል እንዳለ ሰማ፥ ያዕቆብም ልጆቹን፦ ለምን እርስ በርሳችሁ ትተያያላችሁ? አላቸው።

1 Now when Jacob saw that there was corn in Egypt, Jacob said unto his sons, Why do ye look one upon another?

2 እንዲህም አለ፦ እነሆ ስንዴ በግብፅ እንዲገኝ ሰምቼአለሁ ወደዚያ ውረዱ፥ እንድንድንና እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን።

2 And he said, Behold, I have heard that there is corn in Egypt: get you down thither, and buy for us from thence; that we may live, and not die.

3 የዮሴፍም አሥሩ ወንድሞቹ ስንዴን ከግብፅ ይሸምቱ ዘንድ ወረዱ

3 And Joseph’s ten brethren went down to buy corn in Egypt.

4 የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም። ምናልባት ክፉ እንዳያገኘው ብሎአልና።

4 But Benjamin, Joseph’s brother, Jacob sent not with his brethren; for he said, Lest peradventure mischief befall him.

5 የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡቱ ጋር ገቡ በከነዓን አገር ራብ ነበረና።

5 And the sons of Israel came to buy corn among those that came: for the famine was in the land of Canaan.

6 ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ፥ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግምባራቸው ሰገዱለት።

6 And Joseph was the governor over the land, and he it was that sold to all the people of the land: and Joseph’s brethren came, and bowed down themselves before him with their faces to the earth.

7 ዮሴፍም ወንድሞቹን አይቶ አወቃቸው ተለወጠባቸውም፥ ክፉ ቃልንም ተናገራቸው። እናንተ ከወዴት መጣችሁ? አላቸው። እርሱም፦ ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን አሉት።

7 And Joseph saw his brethren, and he knew them, but made himself strange unto them, and spake roughly unto them; and he said unto them, Whence come ye? And they said, From the land of Canaan to buy food.

8 ዮሴፍም ወንድሞቹን አወቃቸው፥ እነርሱ ግን አላወቁትም

8 And Joseph knew his brethren, but they knew not him.

9 ዮሴፍም ስለ እነርሱ አይቶት የነበረውን ሕልም አሰበ። እንዲህም አላቸው፦ እናንተ ሰላዮች ናችሁ የምድሩን ዕራቁትነት ልታዩ መጥታችኋል።

9 And Joseph remembered the dreams which he dreamed of them, and said unto them, Ye are spies; to see the nakedness of the land ye are come.

10 እነርሱም አሉት። ጌታችን ሆይ አይደለም ባሪያዎችህ ስንዴን ሊገዙ መጥተዋል

10 And they said unto him, Nay, my lord, but to buy food are thy servants come.

11 እኛ ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን እኛ እውነተኞች ነን፥ ባሪያዎችህስ ሰላዩች አይደሉም።

11 We are all one man’s sons; we are true men, thy servants are no spies.

12 እርሱም አላቸው። አይደለም ነገር ግን የአገሩን ዕራቁትነት ልታዩ መጥታችኋል።

12 And he said unto them, Nay, but to see the nakedness of the land ye are come.

13 እነርሱም አሉ፦ ባሪያዎችህ አሥራ ሁለት ወንድማማች በከነዓን ምድር የአንድ ሰው ልጆች ነን ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው፥ አንዱም ጠፍቶአል።

13 And they said, Thy servants are twelve brethren, the sons of one man in the land of Canaan; and, behold, the youngest is this day with our father, and one is not.

14 ዮሴፍም አላቸው። እናንተ ሰላዮች ናችሁ ብዬ የተናገርኋችሁ ይህ ነው

14 And Joseph said unto them, That is it that I spake unto you, saying, Ye are spies:

15 በዚህ ትፈተናላችሁ ታናሽ ወንድማችሁ ካልመጣ በቀር የፈርዖንን ሕይወት ከዚህ አትወጡም።

15 Hereby ye shall be proved: By the life of Pharaoh ye shall not go forth hence, except your youngest brother come hither.

16 እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ነገራችሁ ይፈተን ዘንድ ከእናንተ አንዱን ስደዱ፥ ወንድማችሁንም ይዞ ይምጣ እናንተም ታሥራችሁ ተቀመጡ ይህ ካልሆነ የፈርዖንን ሕይወት ሰላዮች ናችሁ።

16 Send one of you, and let him fetch your brother, and ye shall be kept in prison, that your words may be proved, whether there be any truth in you: or else by the life of Pharaoh surely ye are spies.

17 ሦስት ቀን ያህል በግዞት ቤት ጨመራቸው።

17 And he put them all together into ward three days.

18 በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፦ ትድኑ ዘንድ ይህን አድርጉ እኔ እግዚአብሔርን እፈራለሁና።

18 And Joseph said unto them the third day, This do, and live; for I fear God:

19 እናንተ የታመናችሁ ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ ወንድማችሁ በግዞታችሁ ቤት ይታሰር እናንተ ግን ሂዱ፥ እህሉንም ለቤታችሁ ራብ ውሰዱ

19 If ye be true men, let one of your brethren be bound in the house of your prison: go ye, carry corn for the famine of your houses:

20 ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ ይዛችሁ ኑ ነገራችሁም የታመነ ይሆናልና አትሞቱም። እንዲህም አደረጉ።

20 But bring your youngest brother unto me; so shall your words be verified, and ye shall not die. And they did so.

21 እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ። በእውነት ወንድማችንን በድለናል፥ እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።

21 And they said one to another, We are verily guilty concerning our brother, in that we saw the anguish of his soul, when he besought us, and we would not hear; therefore is this distress come upon us.

22 ሮቤልም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ብላቴናውን አትበድሉ ብያችሁ አልነበረምን? እኔም አልሰማችሁኝም ስለዚህ እነሆ አሁን ደሙ ይፈላለገናል።

22 And Reuben answered them, saying, Spake I not unto you, saying, Do not sin against the child; and ye would not hear? therefore, behold, also his blood is required.

23 እነርሱም ዮሴፍ ነገራቸውን እንደሚሰማባቸው አላወቁም፥ በመካከላቸው አስተርጓሚ ነበረና።

23 And they knew not that Joseph understood them; for he spake unto them by an interpreter.

24 ከእነርሱም ዘወር ብሎ አለቀሰ ደግሞም ወደ እነርሱ ተመልሶ ተናገራቸው፥ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ወሰዶ በፊታቸው አሰረው።

24 And he turned himself about from them, and wept; and returned to them again, and communed with them, and took from them Simeon, and bound him before their eyes.

25 ዮሴፍም ዓይበታቸውን እህል ይሞሉት ዘንድ አዘዘ የእየራሳቸውንም ብር በእየዓይበታቸው ይመልሱት ዘንድ ደግሞም የመንገድ ስንቅ ይሰጡአቸው ዘንድ አዘዘ። እንዲሁም ተደረገላቸው።

25 Then Joseph commanded to fill their sacks with corn, and to restore every man’s money into his sack, and to give them provision for the way: and thus did he unto them.

26 እነርሱም እህሉን በአህዮቻቸው ላይ ጫኑ፥ ከዚያም ተነሥተው ሄዱ።

26 And they laded their asses with the corn, and departed thence.

27 ከእነርሱም አንዱ ባደሩበት ስፍራ ለአህያው ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ሲፈታ ብሩን አየ፥ እነሆም በዓይበቱ አፍ ላይ ነበረች።

27 And as one of them opened his sack to give his ass provender in the inn, he espied his money; for, behold, it was in his sack’s mouth.

28 ለወንድሞቹም። ብሬ ተመለሰችልኝ፥ እርስዋም በዓይበቴ አፍ እነኋት አላቸው። ልባቸውም ደነገጠ፥ እየተንቀጠቀጡም እርስ በርሳቸው ተባባሉ። እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ምንድር ነው?

28 And he said unto his brethren, My money is restored; and, lo, it is even in my sack: and their heart failed them, and they were afraid, saying one to another, What is this that God hath done unto us?

29 ወደ አባታቸውም ወደ ያዕቆብ ወደ ከነዓን ምድር መጡ፥ የደረሰባቸውንም ነገር ሁሉ እንዲህ ብለው አወሩ።

29 And they came unto Jacob their father unto the land of Canaan, and told him all that befell unto them; saying,

30 የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው በክፉ ንግግር ተናገረን፥ የምድሪቱም ሰላዮች አስመሰለን።

30 The man, who is the lord of the land, spake roughly to us, and took us for spies of the country.

31 እኛም እንዲህ አልነው፦ እውነተኞች ሰዎች ነን እንጂ ሰላዮች አይደለንም

31 And we said unto him, We are true men; we are no spies:

32 እኛ የአባታችን ልጆች አሥራ ሁለት ወንድማማች ነን አንዱ ጠፍቶአል፥ ታናሹም በከነዓን ምድር ዛሬ ከአባታችን ጋር አለ።

32 We be twelve brethren, sons of our father; one is not, and the youngest is this day with our father in the land of Canaan.

33 የአገሩም ጌታ ያ ሰው እንዲህ አለን፦ የታመናችሁ ሰዎች ከሆናችሁ በዚህ አውቃለሁ አንደኛውን ወንድማችሁን ከእኔ ጋር ተዉት፥ ለቤታችሁም ራብ እህልን ወስዳችሁ ሂዱ

33 And the man, the lord of the country, said unto us, Hereby shall I know that ye are true men; leave one of your brethren here with me, and take food for the famine of your households, and be gone:

34 ታናሹንም ወንድማችሁን አምጡልኝ፥ እውነተኞች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁንም በዚህ አውቀዋለሁ ወንድማችሁንም እሰጣችኋለሁ፥ እናንተም በምድሩ ትነግዳላችሁ።

34 And bring your youngest brother unto me: then shall I know that ye are no spies, but that ye are true men: so will I deliver you your brother, and ye shall traffick in the land.

35 እንዲህም ሆነ ዓይበታቸውን በፈቱ ጊዜ እነሆ ከእነርሱ እያንዳንዳቸው ብራቸውን በእየዓይበታቸው ተቋጥሮ አገኙት እነርሱም አባታቸውም የብራቸውን ቍጥራት አይተው ፈሩ።

35 And it came to pass as they emptied their sacks, that, behold, every man’s bundle of money was in his sack: and when both they and their father saw the bundles of money, they were afraid.

36 አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፦ ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ ዮሴፍ የለም፥ ስምዖንም የለም፥ ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።

36 And Jacob their father said unto them, Me have ye bereaved of my children: Joseph is not, and Simeon is not, and ye will take Benjamin away: all these things are against me.

37 ሮቤልም አባቱን አለው። ወደ አንተ መልሼ ያላመጣሁት እንደ ሆነ ሁለቱን ልጆቼን ግደል እርሱን በእጄ ስጠኝ፥ እኔም ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።

37 And Reuben spake unto his father, saying, Slay my two sons, if I bring him not to thee: deliver him into my hand, and I will bring him to thee again.

38 እርሱም አለ፦ ልጄ ከእናንተ ጋር አይወርድም ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፉ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።

38 And he said, My son shall not go down with you; for his brother is dead, and he is left alone: if mischief befall him by the way in the which ye go, then shall ye bring down my gray hairs with sorrow to the grave.