ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #49
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 49 |
Genesis 49 |
1 ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ በኋለኛው ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ። |
1 And Jacob called unto his sons, and said, Gather yourselves together, that I may tell you that which shall befall you in the last days. |
2 እናንት የያዕቆብ ልጆች ተሰብሰቡ፥ ስሙም አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ። |
2 Gather yourselves together, and hear, ye sons of Jacob; and hearken unto Israel your father. |
3 ሮቤል፥ አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ፥ የጕብዝናዬም መጀመሪያ ነህ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ። |
3 Reuben, thou art my firstborn, my might, and the beginning of my strength, the excellency of dignity, and the excellency of power: |
4 እንደ ውኃ የምትዋልል ነህ አለቅነት ለአንተ አይሁን ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና አረከስኸውም ወደ አልጋዬም ወጣ። |
4 Unstable as water, thou shalt not excel; because thou wentest up to thy father’s bed; then defiledst thou it: he went up to my couch. |
5 ስምዖንና ሌዊ ወንድማማች ናቸው ሰይፎቻቸው የዓመፃ መሣሪያ ናቸው። |
5 Simeon and Levi are brethren; instruments of cruelty are in their habitations. |
6 በምክራቸው፥ ነፍሴ፥ አትግባ ከጉባኤአቸውም ጋር፥ ክብሬ፥ አትተባበር በቍጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክሰዋልና። |
6 O my soul, come not thou into their secret; unto their assembly, mine honour, be not thou united: for in their anger they slew a man, and in their selfwill they digged down a wall. |
7 ቍጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና ኵርፍታቸውም፥ ብርቱ ነበርና በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ። |
7 Cursed be their anger, for it was fierce; and their wrath, for it was cruel: I will divide them in Jacob, and scatter them in Israel. |
8 ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ። |
8 Judah, thou art he whom thy brethren shall praise: thy hand shall be in the neck of thine enemies; thy father’s children shall bow down before thee. |
9 ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል? |
9 Judah is a lion’s whelp: from the prey, my son, thou art gone up: he stooped down, he couched as a lion, and as an old lion; who shall rouse him up? |
10 በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል። |
10 The sceptre shall not depart from Judah, nor a lawgiver from between his feet, until Shiloh come; and unto him shall the gathering of the people be. |
11 ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል፥ የአህያይቱንም ግልገል በወይን አረግ ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም። |
11 Binding his foal unto the vine, and his ass’s colt unto the choice vine; he washed his garments in wine, and his clothes in the blood of grapes: |
12 ዓይኑም ከወይን ይቀላል ጥርሱም ከወተት ነጭ ይሆናል። |
12 His eyes shall be red with wine, and his teeth white with milk. |
13 ዛብሎን በባሕር ዳር ይቀመጣል እርሱም ለመርከቦች ወደብ ይሆናል ዳርቻውም እስከ ሲዶና ድረስ ነው። |
13 Zebulun shall dwell at the haven of the sea; and he shall be for an haven of ships; and his border shall be unto Zidon. |
14 ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው፥ በበጎች ጕረኖም መካከል ያርፋል። |
14 Issachar is a strong ass couching down between two burdens: |
15 ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን ትከሻውን ለመሸከም ዝቅ አደረገ፥ በሥራም ገበሬ ሆነ። |
15 And he saw that rest was good, and the land that it was pleasant; and bowed his shoulder to bear, and became a servant unto tribute. |
16 ዳን በወገኑ ይፈርዳል፥ ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ። |
16 Dan shall judge his people, as one of the tribes of Israel. |
17 ዳን በጐዳና ላይ እንደ እባብ ይሆናል፥ በመንገድም እንደ ቀንዳም እባብ ፈረሱን ከሰኮናው ይነክሳል፥ ፈረሰኛም ወደ ኋላው ይወድቃል። |
17 Dan shall be a serpent by the way, an adder in the path, that biteth the horse heels, so that his rider shall fall backward. |
18 እግዚአብሔር ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ። |
18 I have waited for thy salvation, O Lord. |
19 ጋድን ዘማቾች ይዘምቱበታል እርሱ ግን ተከታትሎ ይዘምትባቸዋል። |
19 Gad, a troop shall overcome him: but he shall overcome at the last. |
20 የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው፥ ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይሰጣል። |
20 Out of Asher his bread shall be fat, and he shall yield royal dainties. |
21 ንፍታሌም የተፈታ ሚዳቋ ነው መልካም ቃልን ይሰጣል። |
21 Naphtali is a hind let loose: he giveth goodly words. |
22 ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ። |
22 Joseph is a fruitful bough, even a fruitful bough by a well; whose branches run over the wall: |
23 ቀስተኞች አስቸገሩት፥ ነደፉትም፥ ተቃወሙትም |
23 The archers have sorely grieved him, and shot at him, and hated him: |
24 ነገር ግን ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል ዓምድ፥ |
24 But his bow abode in strength, and the arms of his hands were made strong by the hands of the mighty God of Jacob; (from thence is the shepherd, the stone of Israel:) |
25 በአባትህ አምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ፥ በጥልቅም በረከት ከታች በሚሠራጭ፥ በጡትና በማኅፀን በረከት። |
25 Even by the God of thy father, who shall help thee; and by the Almighty, who shall bless thee with blessings of heaven above, blessings of the deep that lieth under, blessings of the breasts, and of the womb: |
26 የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮረፍቶችም በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፥ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ። |
26 The blessings of thy father have prevailed above the blessings of my progenitors unto the utmost bound of the everlasting hills: they shall be on the head of Joseph, and on the crown of the head of him that was separate from his brethren. |
27 ብንያም ነጣቂ ተኵላ ነው የበዘበዘውን በጥዋት ይበላል፥ የማረከውንም በማታ ይካፈላል። |
27 Benjamin shall ravin as a wolf: in the morning he shall devour the prey, and at night he shall divide the spoil. |
28 እነዚህም ሁሉ አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው። |
28 All these are the twelve tribes of Israel: and this is it that their father spake unto them, and blessed them; every one according to his blessing he blessed them. |
29 እንዲህ ብሎም አዘዛቸው። እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ |
29 And he charged them, and said unto them, I am to be gathered unto my people: bury me with my fathers in the cave that is in the field of Ephron the Hittite, |
30 እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት። |
30 In the cave that is in the field of Machpelah, which is before Mamre, in the land of Canaan, which Abraham bought with the field of Ephron the Hittite for a possession of a buryingplace. |
31 አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ከዚያ ተቀበሩ ከዚያም እኔ ልያን ቀበርኋት |
31 There they buried Abraham and Sarah his wife; there they buried Isaac and Rebekah his wife; and there I buried Leah. |
32 እርሻውና በእርስዋ ላይ ያለችው ዋሻ ከኬጢ ልጆች የተገዙ ናቸው። |
32 The purchase of the field and of the cave that is therein was from the children of Heth. |
33 ያዕቆብም ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ። |
33 And when Jacob had made an end of commanding his sons, he gathered up his feet into the bed, and yielded up the ghost, and was gathered unto his people. |