ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #16
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 16

Numbers 16

1 የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከሮቤልም ልጆች የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን የፋሌትም ልጅ ኦን በሙሴ ላይ ተነሡ። ች የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን የፋሌትም ልጅ ኦን በሙሴ

1 Now Korah, the son of Izhar, the son of Kohath, the son of Levi, and Dathan and Abiram, the sons of Eliab, and On, the son of Peleth, sons of Reuben, took men:

2 ከእስራኤልም ልጆች ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች ከእነርሱ ጋር ወሰዱ ከጉባኤው የተመረጡ ዝናቸውም የተሰማ የማኅበሩ አለቆች ነበሩ።

2 And they rose up before Moses, with certain of the children of Israel, two hundred and fifty princes of the assembly, famous in the congregation, men of renown:

3 በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው። ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ እግዚአብሔርም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችኋል በእግዚአብሔርም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ? አሉ።

3 And they gathered themselves together against Moses and against Aaron, and said unto them, Ye take too much upon you, seeing all the congregation are holy, every one of them, and the Lord is among them: wherefore then lift ye up yourselves above the congregation of the Lord?

4 ሙሴም በሰማ ጊዜ በግምባሩ ወደቀ

4 And when Moses heard it, he fell upon his face:

5 ለቆሬም ለወገኑም ሁሉ። ነገ እግዚአብሔር ለእርሱ የሚሆነውን፥ ቅዱስም የሚሆነውን ያስታውቃል የመረጠውንም ሰው ወደ እርሱ ያቀርበዋል።

5 And he spake unto Korah and unto all his company, saying, Even to morrow the Lord will shew who are his, and who is holy; and will cause him to come near unto him: even him whom he hath chosen will he cause to come near unto him.

6 እንዲሁ አድርጉ ቆሬና ወገንህ ሁሉ፥ ጥናዎቹን ውሰዱ

6 This do; Take you censers, Korah, and all his company;

7 ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው እንዲህም ይሆናል እግዚአብሔር የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል እናንተ የሌዊ ልጆች ሆይ እጅግ አብዝታችኋል ብሎ ተናገራቸው።

7 And put fire therein, and put incense in them before the Lord to morrow: and it shall be that the man whom the Lord doth choose, he shall be holy: ye take too much upon you, ye sons of Levi.

8 ሙሴም ቆሬን አለው። እናንተ የሌዊ ልጆች፥ ስሙ

8 And Moses said unto Korah, Hear, I pray you, ye sons of Levi:

9 የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር የለያችሁ፥ የእግዚአብሔርንም ማደሪያ አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ፥ እንድታገለግሉአቸውም በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁ አይበቃችሁምን?

9 Seemeth it but a small thing unto you, that the God of Israel hath separated you from the congregation of Israel, to bring you near to himself to do the service of the tabernacle of the Lord, and to stand before the congregation to minister unto them?

10 አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቦአል ክህነትንም ደግሞ ትፈልጋላችሁን?

10 And he hath brought thee near to him, and all thy brethren the sons of Levi with thee: and seek ye the priesthood also?

11 ስለዚህም አንተና ወገንህ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ተሰብስባችኋል በእርሱም ላይ ታጕረመርሙ ዘንድ አሮን ማን ነው?

11 For which cause both thou and all thy company are gathered together against the Lord: and what is Aaron, that ye murmur against him?

12 ሙሴም የኤልያብን ልጆች ዳታንና አቤሮንን እንዲጠሩአቸው ላከ እርሱም፦ አንመጣም

12 And Moses sent to call Dathan and Abiram, the sons of Eliab: which said, We will not come up:

13 በምድረ በዳ ትገድለን ዘንድ ወተትና ማር ከምታፈስሰው ምድር ያወጣኸን አይበቃህምን? ደግመህ በእኛ ላይ ራስህን አለቃ ታደርጋለህን?

13 Is it a small thing that thou hast brought us up out of a land that floweth with milk and honey, to kill us in the wilderness, except thou make thyself altogether a prince over us?

14 ደግሞ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላገባኸንም፥ እርሻና ወይንም አላወረስኸንም የእነዚህንስ ሰዎች ዓይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም አሉ።

14 Moreover thou hast not brought us into a land that floweth with milk and honey, or given us inheritance of fields and vineyards: wilt thou put out the eyes of these men? we will not come up.

15 ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ እግዚአብሔርንም። ወደ ቍርባናቸው አትመልከት እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ ስንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም አለው።

15 And Moses was very wroth, and said unto the Lord, Respect not thou their offering: I have not taken one ass from them, neither have I hurt one of them.

16 ሙሴም ቆሬን። ነገ አንተ፥ ወገንህም ሁሉ፥ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁኑ

16 And Moses said unto Korah, Be thou and all thy company before the Lord, thou, and they, and Aaron, to morrow:

17 ሁላችሁም ጥናዎቻችሁን ውሰዱ፥ ዕጣንም አድርጉባቸው፥ እያንዳንዳችሁም ጥናዎቻችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት አምጡ፥ ሁለት መቶ አምሳ ጥናዎች አንተ ደግሞ አሮንም ጥናዎቻችሁን አምጡ አለው።

17 And take every man his censer, and put incense in them, and bring ye before the Lord every man his censer, two hundred and fifty censers; thou also, and Aaron, each of you his censer.

18 እያንዳንዱም ጥናውን ወሰደ፥ እሳትም አደረገበት፥ ዕጣንም ጨመረበት፥ ከሙሴና ከአሮንም ጋር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቆመ።

18 And they took every man his censer, and put fire in them, and laid incense thereon, and stood in the door of the tabernacle of the congregation with Moses and Aaron.

19 ቆሬም ማኅበሩን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእነርሱ ላይ ሰበሰበ የእግዚአብሔርም ክብር ለማኅበሩ ሁሉ ተገለጠ።

19 And Korah gathered all the congregation against them unto the door of the tabernacle of the congregation: and the glory of the Lord appeared unto all the congregation.

20 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው።

20 And the Lord spake unto Moses and unto Aaron, saying,

21 ሁሉን በቅጽበት አጠፋቸው ዘንድ ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ።

21 Separate yourselves from among this congregation, that I may consume them in a moment.

22 እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው። አምላክ ሆይ፥ አንተ የሰው ሁሉ ነፍስ አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን? አሉ።

22 And they fell upon their faces, and said, O God, the God of the spirits of all flesh, shall one man sin, and wilt thou be wroth with all the congregation?

23 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

23 And the Lord spake unto Moses, saying,

24 ለማኅበሩ። ከቆሬና ከዳታን ከአቤሮንም ማደሪያ ዙሪያ ፈቀቅ በሉ ብለህ ንገራቸው።

24 Speak unto the congregation, saying, Get you up from about the tabernacle of Korah, Dathan, and Abiram.

25 ሙሴም ተነሥቶ ወደ ዳታንና ወደ አቤሮን ሄደ የእስራኤልም ሽማግሌዎች ተከተሉት።

25 And Moses rose up and went unto Dathan and Abiram; and the elders of Israel followed him.

26 ማኅበሩንም። እባካችሁ፥ ከእነዚህ ክፉዎች ድንኳን ፈቀቅ በሉ በኃጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ ለእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ ብሎ ተናገራቸው።

26 And he spake unto the congregation, saying, Depart, I pray you, from the tents of these wicked men, and touch nothing of theirs, lest ye be consumed in all their sins.

27 ከቆሬና ከዳታን ከአቤሮንም ማደሪያ ከዙሪያውም ሁሉ ፈቀቅ አሉ ዳታንና አቤሮንም ሴቶቻቸውም ልጆቻቸውም ሕፃናቶቻቸውም ወጥተው በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ቆሙ።

27 So they gat up from the tabernacle of Korah, Dathan, and Abiram, on every side: and Dathan and Abiram came out, and stood in the door of their tents, and their wives, and their sons, and their little children.

28 ሙሴም አለ። ይህን ሥራ ሁሉ አደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከኝ እንጂ ከልቤ እንዳይደለ በዚህ ታውቃላችሁ።

28 And Moses said, Hereby ye shall know that the Lord hath sent me to do all these works; for I have not done them of mine own mind.

29 እነዚህ ሰዎች ሰው እንደሚሞት ቢሞቱ፥ ወይም እንደ ሰው ሁሉ ቢቀሠፉ እግዚአብሔር አልላከኝም።

29 If these men die the common death of all men, or if they be visited after the visitation of all men; then the Lord hath not sent me.

30 እግዚአብሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ።

30 But if the Lord make a new thing, and the earth open her mouth, and swallow them up, with all that appertain unto them, and they go down quick into the pit; then ye shall understand that these men have provoked the Lord.

31 እንዲህም ሆነ ይህን ቃል ሁሉ መናገር በፈጸመ ጊዜ ከበታቻቸው ያለው መሬት ተሰነጠቀ

31 And it came to pass, as he had made an end of speaking all these words, that the ground clave asunder that was under them:

32 ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ቤተ ሰቦቻቸውንም፥ ለቆሬም የነበሩትን ሰዎች ሁሉ፥ ዕቃዎቻቸውንም ሁሉ ዋጠቻቸው።

32 And the earth opened her mouth, and swallowed them up, and their houses, and all the men that appertained unto Korah, and all their goods.

33 እነርሱም ለእነርሱም የነበሩ ሁሉ በሕይወታቸው ወደ ሲኦል ወረዱ ምድሪቱም ተዘጋችባቸው፥ ከጉባኤውም መካከል ጠፉ።

33 They, and all that appertained to them, went down alive into the pit, and the earth closed upon them: and they perished from among the congregation.

34 በዙሪያቸው የነበሩ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ከጩኸታቸው የተነሣ። ምድሪቱ እንዳትውጠን ብለው በረሩ።

34 And all Israel that were round about them fled at the cry of them: for they said, Lest the earth swallow us up also.

35 እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥታ ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች በላች።

35 And there came out a fire from the Lord, and consumed the two hundred and fifty men that offered incense.

36 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

36 And the Lord spake unto Moses, saying,

37 ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር እንዲህ ብለህ ንገረው። ተቀድሰዋልና ጥናዎቹን ከተቃጠሉት ዘንድ ውሰድ፥ እሳቱንም ወደ ውጭ ጣለው

37 Speak unto Eleazar the son of Aaron the priest, that he take up the censers out of the burning, and scatter thou the fire yonder; for they are hallowed.

38 በኃጢአታቸው ሰውነታቸውን ያጠፉትን የእነዚያን ሰዎች ጥናዎች ጠፍጥፈህ ለመሠዊያ መለበጫ አድርጋቸው በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋቸዋልና የተቀደሱ ናቸው፥ ለእስራኤልም ልጆች ምልክት ይሆናሉ።

38 The censers of these sinners against their own souls, let them make them broad plates for a covering of the altar: for they offered them before the Lord, therefore they are hallowed: and they shall be a sign unto the children of Israel.

39 ካህኑም አልዓዛር የተቃጠሉት ሰዎች ያቀረቡአቸውን የናስ ጥናዎች ወስዶ ጠፍጥፎም ለመሠዊያው መለበጫ አደረጋቸው።

39 And Eleazar the priest took the brasen censers, wherewith they that were burnt had offered; and they were made broad plates for a covering of the altar:

40 በቆሬና በወገኑ የደረሰው እንዳይደርስበት፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እንዳይቀርብ፥ እግዚአብሔር በሙሴ እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።

40 To be a memorial unto the children of Israel, that no stranger, which is not of the seed of Aaron, come near to offer incense before the Lord; that he be not as Korah, and as his company: as the Lord said to him by the hand of Moses.

41 በነጋውም የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ። እናንተ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ገድላችኋል ብለው በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ።

41 But on the morrow all the congregation of the children of Israel murmured against Moses and against Aaron, saying, Ye have killed the people of the Lord.

42 እንዲህም ሆነ ማኅበሩ በሙሴና በአሮን ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ ወደ መገናኛው ድንኳን አዩ እነሆም፥ ደመናው ሸፈነው፥ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠ።

42 And it came to pass, when the congregation was gathered against Moses and against Aaron, that they looked toward the tabernacle of the congregation: and, behold, the cloud covered it, and the glory of the Lord appeared.

43 ሙሴና አሮንም ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት መጡ።

43 And Moses and Aaron came before the tabernacle of the congregation.

44 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

44 And the Lord spake unto Moses, saying,

45 ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ፥ እኔም በቅጽበት አጠፋቸዋለሁ። በግምባራቸውም ወደቁ።

45 Get you up from among this congregation, that I may consume them as in a moment. And they fell upon their faces.

46 ሙሴም አሮንን፦ ጥናህን ውሰድ፥ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፥ ዕጣንም ጨምርበት፥ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው አስተስርይላቸውም ከእግዚአብሔር ፊት ቍጣ ወጥቶአልና መቅሠፍት ጀምሮአል አለው።

46 And Moses said unto Aaron, Take a censer, and put fire therein from off the altar, and put on incense, and go quickly unto the congregation, and make an atonement for them: for there is wrath gone out from the Lord; the plague is begun.

47 አሮንም ሙሴ እንደ ተናገረው ጥናውን ወስዶ ወደ ጉባኤው መካከል ሮጠ እነሆም፥ መቅሠፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር ዕጣንም ጨመረ፥ ለሕዝቡም አስተሰረየላቸው።

47 And Aaron took as Moses commanded, and ran into the midst of the congregation; and, behold, the plague was begun among the people: and he put on incense, and made an atonement for the people.

48 በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ መቅሠፍቱም ተከለከለ።

48 And he stood between the dead and the living; and the plague was stayed.

49 በቆሬም ምክንያት ከሞቱት ሌላ በመቅሠፍቱ የሞቱት አሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።

49 Now they that died in the plague were fourteen thousand and seven hundred, beside them that died about the matter of Korah.

50 አሮንም ወደ ሙሴ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተመለሰ መቅሠፍቱም ተከለከለ።

50 And Aaron returned unto Moses unto the door of the tabernacle of the congregation: and the plague was stayed.