መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #46
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 46

Ps 46

1 አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።

1 God is our refuge and strength, a very present help in trouble.

2 ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።

2 Therefore will not we fear, though the earth be removed, and though the mountains be carried into the midst of the sea;

3 ውኆቻቸው ጮኹ ተናወጡም፥ ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ።

3 Though the waters thereof roar and be troubled, though the mountains shake with the swelling thereof. Selah.

4 የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።

4 There is a river, the streams whereof shall make glad the city of God, the holy place of the tabernacles of the most High.

5 እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል።

5 God is in the midst of her; she shall not be moved: God shall help her, and that right early.

6 አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተመለሱ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።

6 The heathen raged, the kingdoms were moved: he uttered his voice, the earth melted.

7 የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።

7 The Lord of hosts is with us; the God of Jacob is our refuge. Selah.

8 የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ።

8 Come, behold the works of the Lord, what desolations he hath made in the earth.

9 እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነት ይሽራል። ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቈርጣል በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል።

9 He maketh wars to cease unto the end of the earth; he breaketh the bow, and cutteth the spear in sunder; he burneth the chariot in the fire.

10 ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።

10 Be still, and know that I am God: I will be exalted among the heathen, I will be exalted in the earth.

11 የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።

11 The Lord of hosts is with us; the God of Jacob is our refuge. Selah.